




ክቡር ኮሌጅ የአፍሪካ ቢዝነስ ስኩልስ ማህበር /AABS Connect Conference 2025/ በካይሮ ፣ ግብፅ ባዘጋጀው ዓመታዊ ኮንፈረንስ ላይ ተሳተፈ።
የማህበሩ 20ኛ ዓመት በተከበረበት በዚህ ደማቅ መርሃግብር ከ40 በላይ ሀገራት የተወጣጡ ከ100 በላይ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተሳትፈዋል። በኮንፈረንሱ ላይ የክቡር ኮሌጅ ልዑካን የተገኙ ሲሆን ኮሌጁ ከሁለት ዓመት በፊት የሚጠበቅበትን መስፈርት አሟልቶ ያቀረበዉ ጥያቄ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች የተሻለ ተቀባይነት አግኝቶ የ2026 የማህበሩ ዓመታዊ ጉባኤ በክቡር ኮሌጅ አዘጋጅነት ኢትዮጲያ እንድታካሄድ ተመርጣለች። እንኳን ደስ አለን!!🎉
በተጨማሪም ክቡር ኮሌጅ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጋራ የሚሰራበትን ሁኔታ የተወያየ ሲሆን በቀጣይም ጉባኤው በአዲስ አበባ ሲካሄድ ስለሚኖረዉ ሁኔታ ከባለድርሻ አካላት እየተነጋገረ ሲሆን በቀጣይ በዚህ ሀገራዊ ሁነት በተመለከተ ዝርዝር መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል።
