
ክቡር ኮሌጅ የአፍሪካ ቢዝነስ ስኩልስ ማህበር /AABS Connect Conference 2023/ በአክራ፣ ጋና ባዘጋጀው ዓመታዊ ኮንፈረንስ ላይ ተሳተፈ።
“የአፍሪካ ቢዝነስ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአፍሪካ ያላቸውን ሚና እና አስተዋፅኦ “መሪ ሃሳብ አድርጎ በተካሄደው ኮንፍረንስ ከ30 ሀገራት የተውጣጡ ከ መቶ በላይ የቢዝነስ ትምህርት ቤቶች እና የትምህርት ተቋማት ተሳትፈዋል። በኮንፈረንሱ ላይ የክቡር ኮሌጅ ዲን አቶ ደሳለኝ መኩሪያ “የአፍሪካ የቢዝነስ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወደፊት ተግዳሮትና የወደፊት ዕጣ ፈንታ” በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል::
በተጨማሪም ክቡር ኮሌጅ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጋራ የሚሰራበትን ሁኔታ የተወያየ ሲሆን በቀጣይም ጉባኤው በአዲስ አበባ የሚካሄድበት ሁኔታ መክሯል::
Kibur College recently participated in the annual AABS connect conference 2023, held at the GIMPA in Accra, Ghana.
Business schools and educational institutions from 30 countries have participated in the conference under the theme “Are Business Schools Relevant in Africa?”. During the conference, Kibur College Dean, Desalegn Mekuria, deliver a presentation in a panel discussion on the topic of “The Future of Africa business schools.”
Besides, kibur discussed with various institutions to collaborate on wide-ranging issues.

